ይህ ንግግር የፍሬድሪክ ኒቼ ነው። እንደሚታወቀው ኒቼ የክርስትና ተቃዋሚ የነበረ ሰው ነው። ይህ አባባሉ ግን በብዙ መልኩ እውነት ሆኖ እናገኘዋለን። ጓደኛዬ @muhammad_ewnetlehulu ያኔ አገልግሎት ሲጀምር የመከርኩት አንድ ምክር ነበር። እየተፋለምነው ያለነውን ንፅረተ-ዓለም መጻሕፍት ስናነብ አእምሯችን ክፋትን እንዳይላመድ መጠንቀቅ ይኖርብናል። ከሰው ልጆች አደገኛ ባሕርያት መካከል አንዱ ክፋትንም ሆነ መልካምነትን መላመዱ ነው። እጅግ መልካም የሆነ ወይም የተወደደ ነገር በጊዜ ሒደት ለምደነው ሊያሰለቸን ይችላል። እጅግ በጣም ክፉ የሆነ ነገር ደጋግመን ስንመለከተው እንደ ቀላል ነገር ሊታየን ይችላል። እናም ተወዳጆች ሆይ አእምሯችን ክፋትን ተላምዶ ሰብዓዊነታችንን እንዳንነጠቅ ሁል ጊዜ ራሳችንን እንፈትን። በሚያሳዝነው ማዘን፣ በሚያስደነግጠው መደንገጥ፣ የሚያስፈራውን መፍራት፣ የሚያፀይፈውን መፀየፍ፣ በሚያስቆጣው መቆጣት መቻል አለብን። ክፋትን እየተመለከትን ምንም የተለየ ስሜት ካልተሰማን (indifferent ከሆንን) ችግር ላይ መውደቃችን ገብቶን ራሳችንን ልናነቃ ይገባናል።
#ewentlehulu #foryou #iyesus #habashatiktok #ethiopian_tik_tok #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር✝️❤
#ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#Ethiopia #protestantmezmur #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር
#fyp