መዝሙር 34 1: አቤቱ፥ የሚበድሉኝን በድላቸው፥የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው። 2: ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥እኔንም ለመርዳት ተነሥ። 3: ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ፤ነፍሴን፦ “መድኃኒትሽ እኔ ነኝ፡” በላት። 4: ነፍሴን የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቍሉም፤ ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይፈሩ፡ወደ ኋላቸውም ይበሉ። 5: በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ፥ የእግዚአብሔርም መልአክ ያስጨንቃቸው። 6: መንገዳቸው ዳጥና ጨለማ ይሁን፥ የእግዚአብሔርም መልአክ ያሳድዳቸው። 7: በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና፥ ነፍሴን በከንቱ አበሳጭተዋልና። 8: ያላወቁት ወጥመድ ይምጣባቸው፥ የሸሸጉትም ወጥመድ ይያዛቸው፤በዚህ ወጥመድ ውስጥ ይውደቁ። 9: ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፥ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች። 10: አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው?ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥ ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።” 11: የክፋት ምስክሮች ተነሡብኝ፥የማላውቀውንም በእኔ ላይ ተናገሩ። 12: ስለ በጎ ክፋትን መለሱልኝ፥ነፍሴንም ልጆችን አሳጡአት። 13: እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፤ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ። 14: ለወዳጄና ለወንድሜ እንደማደርግ አደረግሁ፤ለእናቱም እንደሚያለቅስ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ። 15: በእኔ ላይ ተሰበሰቡ ደስም አላቸው፤ ግፈኞች በእኔ ላይ ተሰበሰቡ እኔም አላውቅሁም፤ ቀደዱኝ አልተውኝምም። 16: ፈተኑኝ በሣቅም ዘበቱብኝ፥ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቅጩ። 17: አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ታይልኛለህ? ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው፡ብችነቴንም ከአንበሶች አድናት። 18: አቤቱ፥ በታላቁ ጉባኤ ውስጥ እገዛልሃለሁ፥ በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግንሃለሁ። 19: በግፍ የሚጠሉኝ በላዬ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጣሉኝም በዓይናቸው አይጣቀሱብኝ። 20: ለእኔስ ሰላምን ይናገሩኛልና፥በቍጣም ሽንገላን ይመክራሉ። 21: አፋቸውንም በእኔ ላይ አላቀቁ፤እሰይ እሰይ፥ ዓይናችን አየው ይላሉ። 22: አቤቱ፥ አንተ አየኸው፤ዝም አትበል፤አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ። 23: አምላኬ ጌታዬም፥ ወደ ፍርዴ ተነሥ፥ አቤቱ፥ ፍርዴን አድምጥ። 24: አቤቱ አምላኬ፥ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፥ በላዬም ደስ አይበላቸው። 25: በልባቸው፦ “እሰይ እሰይ፥ ነፍሳችንን ደስ አላት፡” አይበሉ፤ደግሞም፦ “ዋጥነው፡”አይበሉ። 26: በመከራዬ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፥ በአንድነትም ይጐስቍሉ፤በእኔ ላይ የሚታበዩ እፍረትንና ጕስቍልናን ይልበሱ። 27: ጽድቄን የሚወድዱአት ደስ ይበላቸው ሐሴትንም ያድርጉ፤ የባሪያውን ሰላም የሚወድድ እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን ዘወትር ይበሉ። 28: ምላሴ ጽድቅህን፡ሁልጊዜም ምስጋናህን ይናገራል።#እየሱስ_የነብስም_የስጋም_ፈውስ_ነው @ሐዋርያዊ መልሶች - Apostolic Answers