#ከእኔ_ተማሩ #የፊልጵስዩስ_ትምህርት (ቀን 6) ዋና ርዕስ:- ደስተኞች ሁኑ ንዑስ ርዕስ:- ደስታዬን ፍፁም አድርጉልኝ 📖 ፊል 2:1-4 - የአንድ አማኝ ጤናማ ደስታ የኔ የሚለው ነገር ሲነካ ጤና የሚያጣበት ሳይሆን ቤ/ክ ስትነካ የሚያመው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ደስታው ሲሆን፣ ወንጌል ሲነካ የሚሠማው፤ ቅዱሳን ሲነኩ የሚያመው ሲሆን ነው። - ቤተክርስቲያን ስትነካ ምንም ካልተሠማን፣ የያገባኛል ስሜት ከሌለን፤ ይመለከተኛል ካላልን፣ ተቆርቋሪ ካልሆንን ህመም ነው። 📍ትዕቢት (ቁ.3) - ትዕቢት መነሻው ዲያቢሎስ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ የተደረገለት (የነበረው ስፍራ) ነው። - ትዕቢተኛ ይደነፋል፣ ይነፋል፣ ይወጠራል ግን አንዳች አያውቅም፤ እንዲህ በሆነ ቁጥር አለማወቁን እያሳየ ነው። << ንብ ነድፋው ሰውነቱ የተወጠረውንና የተነፋውን ሠው አምሮብሀል ትሉታላችሁ 😂 በትዕቢት የተወጠረም ሰው ልክ እንደዚሁ ነው>> - ትዕቢት በመጀመሪያ የሚያስለቅቀን ስፍራችንን ነው። ትዕቢተኛ አይሰነብትም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ትዕቢተኛን ይቃወማል። ➥ የትዕቢት መገለጫዎች - ከንቱ ትምክህት - ሌሎችን ማኮሰስ - የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያስብ (ስለሌላው ግድ የማይለው) - ስለሌሎች ምንም ደንታ የሌለው - ንቀት 📖 ሉቃ 18:9 - በዚህ ክፍል የሚታየው ፈሪሳዊ ይጸልያል፣ ይጦማል፣ አስራት ያወጣል፤ ጻድቅ ሆኖ የተቆጠረው ግን ቀራጩ ነው። - ትዕቢተኛ ራሱን ሙሉ አድርጎ ያስባል ሌላውን ግን ያንቃል። - ነግዶ፣ ተምሮ፣ አገልግሎ አንዳች ትምክህት የሚታይበት ሌላውን ያውካል። - ትዕቢት አመፅ ነው፤ ሠውን ኃይለኛና ደንፊ ያደርገዋል ፤ እንደእነዚህ አይነት ሰዎች ቤተክርስቲያን ሲኖሩ ያውካሉ። - ጠቃሚ ሰው፣ ስለሌሎች የሚኖር፣ በዙሪያው ላሉት እንደውሀ የሚያረሠርስ፣ ለፍሬአቸው የሚተጋ፣ የሚያለመልም፣ በብዙ የተሳካለት ያድርገን። - ሌላውን ከእኔ ይበልጣል ብሎ ማሠብ፣ ስፍራውን ለሌላ መስጠት በረከት ነው። - ፉክክር አልተለቀቅንም ስለዚህ በሌላ ሠው ስኬት ልንደሰት ይገባናል፤ የሌላ ሰው ስኬት ስቃይ ሊሆንብን አይገባም። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት ት/ቤት አጠገብ ☎️ +251118633493 📱+251 973 422024