እንኳን ደስ አለን የሳሙኤል አወቀ ልጆች አንድ ሆኑ‼️ ከአንድ ዓመት በላይ በድርጅታዊ ልዩነት ምክንያት በተለያየ ጎራ ተሰልፈው የነበሩ ታጋዮች ልዩነታቸውን አስወግደው ጥላቻን በፍቅር ቀይረው ለተፈጠሩ ችግሮች ይቅር በመባባል በአማራ ፋኖ በጎጃም አደረጃጀት ውስጥ በጋራ ተዋህደው ለመታገል ተስማሙ። በጎንቻ እና አካባቢው ከአማራ ፋኖ በጎጃም ውጭ ማለትም የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት በሚል ይንቀሳቀሱ የነበሩ ከ150 በላይ ፋኖዎች በነበረው ድርጅታዊ ልዩነት ምክንያት ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶችን ያለምንም ቅድመሁኔታ ይቅር በመባባል በዛሬው ዕለት የእርቅ ስነስርዓት ተፈፅሟል። የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት እና በቀጠናው ያለውን ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦርን ድጋፍ ለማድረግ የተመደቡት አርበኛ እሸቱ ጌትነት እና አርበኛ አማረ ቢያዝን ለ(5)ወር ያሕል ጉዳዩን ለመፍታት ውጣውረዱን ያለፈ ሲሆን በመጨረሻ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከአርበኛ የቆየ ሞላ ጋር በመሆን የእርቅ ስነስርዓቱን በሁለቱም ወገን ካሉ መካከለኛ አመራሮች ጋር ፈፅመዋል። በቀጣይም በአማራ ፋኖ በጎጃም ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር አረንዛው ጎንቻ ብርጌድ ስር የሚገኙ ሻለቆች የመዋቅር ሪፎርም እንደሚደረግ ተነግሯል። Eshetu Getnet አርበኛ ፋኖ የቆየ ሞላ አማረ ቢያዝን Hailemichael Bayeh. የድካማችሁ ውጤት።
#californiafire #ፋኖመከታቺን💚💛❤💪💪✅ቤተአማራ💚💛❤✊💒❤🤝❤🕌 #መረጃቲቪ #አማራዬ💚💛❤አማራዬ💚💛❤ #ፋኖ❤️🇪🇹 #ፋኖ_ኩራታችን
#fanon